ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም ጅማ
ለ2018 ዓ.ም ለክረምት በጎ አድራጎት ስራ ጅማ ከተማ የሚገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች ከከተማው ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመር ጋር በመሆን በከተማው ወንዝ ዳርቻ በሚገኝ የሸንኮሬ ፓርክ የችግኝ ተከላ አካሄዱ። በችግኝ ተከላው ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና ከጅማ ቅ/ጽ/ቤት የተውጣጡ 200 ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን 2000 ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ችግኞች ተክለዋል።




