Home / ስለ ኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት / የስራ ክፍል
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በተለያዩ ዘርፎች ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን የመሰብሰብና የመተንተን ኃላፊነት ያላቸው ልዩ ልዩ ክፍሎች የተዋቀረ ተቋም ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ →
የሕዝብ እና የቤት ቆጠራዎችን፣ የናሙና ጥናቶችን በማካሄድ እንዲሁም ከአስተዳደር የመረጃ ምንጮች ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን በመሰበስሰብ፣ በማጠናቀርና በመተንነተን ለመረጃ ተጠቃሚዎች የማቅረብ ኃላፊነት አለበት። ተጨማሪ ያንብቡ →
የስርዓተ ጾታና የአካል ጉዳተኝነት፣ የማህበራዊ አና አስተዳደራዊ ስታቲስቲክስ መረጃዎችን ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ በመሰብሰብ፣ በማጠናቀር እና በመተንተን ጥራታቸውን የጠበቁ… ተጨማሪ ያንብቡ →
የስራ ክፍሉ ቀዳሚ ተግባር ከአስተዳደራዊ የሲቪል ምዝገባ የሚገኙ መረጃዎችን ጥራቱ ወደ ጠበቀ በመዝገብ ላይ የተመሠረተ ስታቲስቲካዊ መረጃ በመለወጥ ለተጠቃሚዎች ማቅረብ ነው። ተጨማሪ ያንብቡ →
ዘመናዊ የጥናት ሜቶዶሎጂዎችን በመቅረጽ እና አማራጭ የመረጃ ምንጮችን ከስታቲስቲክስ ስራ ጋር በማቀናጀት ሀገራዊ ፖሊሲዎች በጥራትና በማስረጃ ላይ ተመስርተው እንዲቀረጹ ያደርጋል። ተጨማሪ ያንብቡ →
ዘርፉ የጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓትን (GIS) እና ሪሞት ሴንሲንግ (Remote Sensing) ከብሔራዊ የስታቲስቲክስ ሥርዓት ጋር በማዋሃድ ጥሬ መረጃዎችን ወደ መገኛ ቦታ ተኮር ዕውቀት ይቀይራል። ተጨማሪ ያንብቡ →
ለአገራዊ ደህንነት ክትትል፣ ለድህነትና የስራ አጥነትን ለመቀነስ ስትራቴጂዎች እና በማስረጃ ላይ ለተመሰረተ የፖሊሲ እቅድ መሠረት የሚሆኑ ጥራት ያላቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን ማቅረብ። ተጨማሪ ያንብቡ →
የስታቲስቲክስ መረጃ ቅንጅት፣ ስታንዳርድና ጥራት የስታቲስቲክስ ስታንዳርዶችን በመቅረጽ፣ ከጥናቶች፣ ቆጠራዎች እና አስተዳደራዊ መዝገቦች የሚገኝ መረጃ ጥራትና ወቅታዊነት እንዲረጋገጥ በማድረግ እና በዓለም ባንክ ውጤት ተኮር ፕሮግራሞች (PforR) ላይ እንደ ገለልተኛ አረጋጋጭ በማገልገል ላይ ያተኮረ ክፍል ነው። ተጨማሪ ያንብቡ →
የስታቲስቲክስ ጥናትና ምርምር እና ስልጠና የስራ ክፍል የስታቲስቲክስ ሜቶዶሎጂን በጥናትና ምርምር ማዘመን/ማሻሻል እና የስታቲስቲክስ ስልጠናዎችንበማስተባበር ተቋማዊ አቅምን የመገንባት ሃላፊነት አለበት። ተጨማሪ ያንብቡ →
የስታቲስቲክስ መረጃ ስርጭት እና ተደራሽነት ከናሙና ጥናቶች፣ ከቆጠራዎች እና ከአስተዳደራዊ መረጃ ምንጮች የሚመነጩ መደበኛ የስታቲስቲክስ መረጃዎች ለተጠቃሚዎች በወቅቱ ይፋ እንዲሆኑ፣ በቀላሉ እንዲደርሱ እና ለአጠቃቀም ቀላል እንዲሆኑ ያደርጋል። ተጨማሪ ያንብቡ →