የስነ ሕዝብ ስታቲስቲክስ መሪ ሥራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት (አ.ስ.አ) ስር ካሉት ዋና ዋና የስራ ክፍሎች አንዱ ሲሆን የሕዝብ እና የቤት ቆጠራዎችን፣ የናሙና ጥናቶችን በማካሄድ እንዲሁም ከአስተዳደር የመረጃ ምንጮች ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን በመሰበስሰብ፣ በማጠናቀርና በመተንነተን ለመረጃ ተጠቃሚዎች የማቅረብ ኃላፊነት አለበት።


የዋና ሥራ አስፈፃሚው ዋና ዓላማ ከሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ፣ የናሙና ጥናቶች፣ የአስተዳደር ስታቲስቲክስ የመረጃ ምንጮች እና ሌሎች የሕዝብ መረጃ ምንጮች ሳይንሳዊ ዘዴዎችን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን፣ ወቅታዊ እና አስተማማኝ የስነሕዝብ እና ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ስታቲስቲክስን መሰብሰብ፣ ማጠናቀር እና መተንተን እና ውጤቱን ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ለሌሎች የስታቲስቲክስ መረጃ ተጠቃሚዎች ዘመናዊና ተስማሚ የመረጃ ስርጭት ዘዴዎችን በመጠቀም  ማቅረብ ነው።