ለአገራዊ ደህንነት ክትትል፣ ለድህነትና የስራ አጥነትን ለመቀነስ ስትራቴጂዎች እና በማስረጃ ላይ ለተመሰረተ የፖሊሲ እቅድ መሠረት የሚሆኑ ጥራት ያላቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን ማቅረብ።


የቤተሰብ በጀትና የስራ ስምሪት ስታቲስቲክስ የተቋቋመው የህዝቡን የኑሮ ደረጃ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለመለካት ነው። ይህ የሥራ ክፍል ዋና ዓላማ በተለይ የሥራ ገበያ፣ የቤተሰብ ፍጆታና ወጪ፣ የድህነት ቁጥጥር እና የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ አመላካቾችን በማዘጋጀት፣ የቤተሰብን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በትክክል በመሰብሰብ፣ መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት ለልማት አገራዊ መፍትሄዎችን ለመንደፍ፣   ለፖሊሲ ውሳኔ፣ ለልማት እቅድ እና ለማህበራዊና ኢኮኖሚ አስተዳደርና ልማት የሚጠቅሙ ትክክለኛና ዘመናዊ መረጃዎችን በማመንጨት የሀገር የስታቲስቲካዊ ልዕልና ማጠናከር ነው።