የግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ
ተግባራትና ኃላፊነቶች
- • ጥናቶችና ቆጠራዎችን ሥራዎች ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ በመምራትና በማስተባበር ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ የሰብል ስታቲስቲክስ፣ የእንስሳት ስታቲስቲክስ፣ የንግድ እርሻዎችና የከተማ ግብርና ስታቲስቲክስ እንዱሁም የአካባቢ፣ የደን እና የመሬት አጠቃቀም ስታቲስቲክስ ጥናትና ቆጠራዎች የቅድመ ዝግጅት ማድረግ፣ የመስክ ሥራ ጥራት ክትትልና ግምገማ ሥራዓት መዘርጋት፤ ለግብርና ስታቲስቲክስ ጥናቶችና ቆጠራዎች የሚያገለግሉ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች እንዲዘጋጁ ማድረግና መከታተል፤ ለውሂብ ስብስብ፣ ግምትና ትንተና ማድረግና የተሟላ የስታቲስቲክስ ስርዓቶችን መተግበር
- • አዳዲስ የስታቲስቲክስ አገማመት ስሌቶች (Statistical Estimation Procedures) እንዲተገበሩ ማድረግ፤ የግብርና ስታቲስቲክስ ጥናት/ምርምር ውጤቶችና ግኝቶችን /Survey results and findings/ ለተጠቃሚዎች በወቅቱ እንዲደርሱ ማስቻል፤ ደረጃቸውን የጠበቁ በሰብል ስታቲስቲክስ፣ በእንስሳት ስታቲስቲክስ፣ በንግድ እርሻዎችና ከተማ ግብርና ስታቲስቲክስ እንዲሁም በአካባቢ፣ ደን እና መሬት አጠቃቀም ስታቲስቲክስ በሚካሄዱ የተለያዩ የጥናት ውጤቶች፣ የጥልቅ ትንተና/in-depth analysis/ ግኝቶችን/findings/ እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
- • በውሂብ ስርዓቶች ውስጥ ፈጠራን መመራት፣ ይህም አስተዳደራዊ ውሂብ፣ ሪሞት ሴንሲንግ፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ዲጂታል የውሂብ ስብስብ መሳሪያዎችን በማቀናጀት ለመረጃ ተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ
- • በመረጃ ላይ ተመስርቶ ለውሳኔ የሚረዱ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች ማቅረብ
የስራ ሂደት የግብርና ስታቲስቲስክ አስመልክቶ
የግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚው ሀጋሪዊ ተሞክሮችና ከምርጥ አለም አቀፍ ልምዶች ጋር የተጣጣመና የተዋቀረ የስታቲስቲክስ የስራ ሂደትን ይከተላል፦
እቅድና ዲዛይን
- • የመረጃ ፍላጎቶችን ከባለደርሻ አካላትና የመረጃ ተጠቃሚዎችን መለየት ያቅዳል ዲዛይን ያደርጋል፡፡
- • የጥናትቶች ፕላትፎርሞች መጠይቆች፣ ኤሌትሮኒክ የዳታ መሰብሰባቢች ቱሎችና የጥናት እቅዶችን ማዘጋጀት
የመስክ የግብርና መረጃ አሰባሰብ በተመለከተ
- • በተሟላ ስልጠና ያገኙ መረጃ ሰብሳቢዎች፣ ሱፐርቫይዘሮችና ስታቲስቲሺያኖች በመጠቀም የግብርና መረጃዎችን ከመስክ ይሰበስባል፣ የተሰበሰቡ መረጃዎችን መስክ ላይ በመሆን ይፈትሻል፣ ግብረ መልሶችን ይልካል፡፡
- • የሳተላይት መረጃዎችን በመጠቀም የግብርና ስታቲስቲክስ አሰባሰብ ማዘመን
- • የመርጃ አሰባሰቡን ቴክኒክ በትራኪንግ ሲስተም ይከታተላል፣በየወቅቱ ይገመግማል፣ ግብረመልስ ይሰጣል
መረጃን ማቀናጀት
- • በመስክ ቦታ ላይ የሚሰጥ ፈጣን ግብረመልስ (feedback) እና መረጃው ከቦታ መስበሰቡን ማረጋገጥ
- • የስታቲስቲክስ ግምት ቴክኒኮችን መተግበር
ትንተና
- • ዋና መለኪያዎች (ምርት፣ ምርታማነት፣ የእንስሳት፣የከባቢናየደን ስታቲስቲክስ) መረጃዎችን ማመንጨት
- • ጥልቅ ትንታኔዎችን መስራት
ስታቲስቲካል መረጃዎችን ማመንጨትና ማሰራጨት በተመለከተ
- • ሪፖርቶች፣ ብለቲኖችና ዳታቤዝ ማቅረብ
- • ከተጠቃሚዎች፣ ሚዲያና ፖሊሲ አውጪዎች ጋር መገናኘት
ግምገማና ማሻሻያ
- • ድህረ ቆጠራ ሰርቬዎች እና የጥራት ግምገማየመስክ መረጃ አሰባሰብ ዘዴዎችን በየጊዜውና በቀጣይነት ባለው መልኩ ማሻሻል
የናሙና እና ቆጠራ አስመልክቶ
የግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ የተሟላና ወቅቱን ያማከለ የግብርና ስታቲስትክስ መረጃ አሰባሰብ ስርዓት ይፈጽማል፦
የናሙና ሰርቬዎች
- • የመሀር ወቅት፣የበልግ ወቅት፣የእንስሳት፣የንግድና ሌሎች እርሻዎች፣የከተማ ግብርና ጥናቶች
- እነዚህ ሰርቬዎች የሚሰጡት፦
- • የሰብል ምርትና ምርታማነት፣ የግብአት አጠቃቀም፣የመሬት አጠቃቀም የመሳሰሉ ጥልቅ መረጃዎች
- • የእንስሳት ብዛት እንዲሁም በአይነት፣ ከእንስሳት ምርት የተገኘ፣ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት አጠቃቀም ጥልቅ መረጃዎች ማመንጨት
የግብርና ቆጠራ
- • ከ22 አመት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን የሚከተሉትን ዋና መረጃዎች ይገኙበታል፡፡
- • ለቀጣይ ሰርቬዎች የናሙና መሰረት ይሆናል
- • መረጃው የመጀመሪያ ድራፍት ሪፓርት ለስትሪንግ ኮሚቴ ቀርቦ ግምገማ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡
የግብርና ስታቲስቲክስ ውጤቶች
የግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰፊ የሆነ የኦፊሴላዊ የግብርና ስታቲስቲክስ ውጤቶችን ያቀርባል፦
- • የሰብል ምርት ስታቲስቲክስ ሪፖርቶች (በክልልና በዞን ደረጃ አካባቢ፣ ምርትና ምርታማነት)
- • የእንስሳት ስታቲስቲክስ (ብዛት፣ አይነት ፣ምርትና አጠቃቀም (በክልልና በዞን ደረጃ አካባቢ፣ ምርትና ምርታማነት)
- • የግብርና ስታቲስቲክስ የታይም ሲሪየስ መረጃዎችን ያቀርባል፡፡
- • ለሀገር ውስጥና ለአለም አቀፍ ሪፖርቲንግ የሚሆኑ መረጃዎችን ያቀርባል፡፡
- • ከላይ የተገለጹትን የግብርና ስታቲስቲክስ ውጤቶች በጥራት፣ትክክለኛነት፣ተመጣጣኝነትናግልጽነት መርህ መሰረት በማድረግ ይዘጋጃሉ።
የግብርና ስታቲስቲካል መረጃዎች ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት
የግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ የግብርና ስታቲስቲክስ ውጤቶች ለሚከተሉት ሀገራዊ ፖሊሲዎች አስፈላጊ ናቸው፦
- • የምግብ ዋስትናና ራስ-በራስ የመቻል ክትትል
- • የማክሮ ኢኮኖሚ እቅድና የግብርና ፖሊሲ ድጋፍ
- • የኢንቨስትመንት ውሳኔዎችና የልማት ፕሮግራሞች