የማህበራዊና አካቶ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ
የስራ ክፍሉ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ የስርዓተ ጾታና የአካል ጉዳተኝነት፣ የማህበራዊ አና አስተዳደራዊ ስታቲስቲክስ መረጃዎችን ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ በመሰብሰብ፣ በማጠናቀር እና በመተንተን ጥራታቸውን የጠበቁ፣ ወቅታዊና አስተማማኝ የሆኑ ስታቲስቲካል የመረጃ ውጤቶችን በተለያየ ሪፖርት መልክ በማዘጋጀት ለመንግስት ተግባራት፣ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች፣ ለተመራማሪዎች እና ለሌሎች መረጃ ተጠቃሚዎች እንዲሰራጩ ማድረግ ነው።
በሥራ ክፍሉ የሚያከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
የስራ ክፍሉ ከአጠቃላይ ቆጠራ፣ ከናሙና ጥናት፣ ከአስተዳደር መዛግብት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የማህበራዊና የትምህርት፣ የአመጋገብ ፣የአስተዳደር፣ የሰላምና የደህንነት፣ የወንጀል ፣ የሥርዓተ-ፆታ፣ የአካል ጉዳተኝነት እና ዓመታዊ የስታቲስቲካል አብስትራክት፣ ወቅታዊና ተዓማኒ መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ በማጠናቀር እና በመተንተን ለተለያዩ መረጃ ተጠቃሚዎች እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡