የስታቲስቲክስ መረጃ ቅንጅት፣ ስታንዳርድና ጥራት መሪ ሥራ አስፈጻሚ በሁለት ዴስኮች ማለትም የስታቲስቲክስ መረጃ ጥራትና ስታንዳርድ ዴስክ እና የፕሮግራም ማረጋገጫ /Program Verification Desk/ የተዋቀረ እና የስታቲስቲክስ፣ የጂ.አይ.ኤስ እና የኮምፒውተር ፕሮግራመር ባለሙያዎች የተዋቀረ ክፍል ነው። ይህ መሪ ሥራ አስፈፃሚ የስታቲስቲክስ ስታንዳርድን በመቅረጽ፣ የስታቲስቲክስ መረጃ አቅርቦት እና ጥራትና ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራትን ይመራል፣ ያስተባብራል። ይህ የስራ ክፍል ከናሙና ጥናቶች፣ ከቆጠራዎች እንዲሁም ከአስተዳደራዊ መዝገቦች የሚመነጭ የስታቲስቲክረስ መረጃ በተቀናጀ ሁኔታ ጥራቱን እና ወቅቱን የጠበቀ እንዲሆን፤ በስታቲስቲክስ ተግባራት ላይ የሚተገበሩ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ጥራት የማረጋገጥ ተግባራትን ይመራል፣ ያስተባብራል። በተጨማሪም ተቋሙ ገለልተኛ አረጋጋጭ በመሆን በተለያዩ ዘርፎች የሚተገበሩ ውጤት ተኮር ፕሮግራሞችን (PforR) የማረጋገጥ ወሳኝ ኃላፊነት ይወጣል። ስለሆነም ጥራት እና ደረጃቸውን የጠበቁ የማረጋገጫ ሪፖርቶችን ለማቅረብ በጋራ የተስማሙባቸውን ደረጃቸውን የጠበቁ የማረጋገጫ ሥነ-ዘዴዎችን በመጠቀም በመረጃ ላይ የተመሠረተ ልማት እንዲፋጠን እና በውጤት ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ፍሰት እንዲቀላጠፍ ተቋሙ ኃላፊነቱን እንዲዎጣ በከፍተኛ ትጋት እየሰራ ይገኛል።


የስታቲስቲክስ ደረጃዎችን በማቀናጀት እና በውጤት ላይ ለተመሰረቱ ፕሮግራሞች ላይ ገለልተኛ አረጋጋጭ በመሆን ቁልፍ አገልግሎት በመስጠት የስታቲስቲክስ ልህቀትን እና ተዓማኒነትን በሥርዓት ለመገንባት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት፤