የስታቲስቲክስ ጥናትና ምርምር እና ስልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት (ኢ.ስ.አ) በስታቲስቲክስ ሲስተም
ልማትና ሜቶዶሎጂ ዘርፍ ስር ከተዋቀሩ መሪ ስራ አስፈጻሚዎች አንዱ ሲሆን በ2016 ዓ.ም በተቋሙ የተደረገውን የመዋቅር ማሻሻያ
ተከትሎ የተመሰረተ ነው። ክፍሉ የስታቲስቲክስ ሜቶዶሎጂን በጥናትና ምርምር ማዘመን/ማሻሻል እና የስታቲስቲክስ ስልጠናዎችን
በማስተባበር ተቋማዊ አቅምን የመገንባት ሃላፊነት አለበት።


የስታቲስቲክስ ጥናትና ምርምር እና ስልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዋና ዓላማዎች፡-

ከዋና ዋና ተግባራት አንዱ ያሉትን የስታቲስቲክስ ናሙና ጥናቶች እና ቆጠራዎች ስነዘዴዎችን በመገምገም ለናሙና አመራረጥ፣ ለስትራቲፊኬሽን
እና ለግመታ ሂደቶች አዳዲስ ስነዘዴዎችን ማዘጋጀትና ያሉትን ማዘመን/ማሻሻል፤ የተለያዩ ሞዴሎችን እና አዳዲስ ሜቴዶሎጂዎችን በማዘጋጀት
እንዲሁም ያሉትን በማሻሻል ለዝቅተኛው የአስተዳደር እርከን/small area estimation እና የትንበያ/projection ሞዴሎችንና ቴክኒኮችን
ማዘጋጀት፣ ማስተዋወቅ፤ የስታቲስቲክስ መረጃ ጥራት እና ተነጻጻሪነትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስነዘዴዎች ላይ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፤
ለአማራጭ የመረጃ ምንጮች የሚሆኑ የስታቲስቲክስ ስነዘዴዎችን በጥናትና ምርምር ማዘመን፤ እና ዓለም አቀፍ የስታቲስቲክስ ምርጥ
ተሞክሮዎችን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከብሄራዊ ሁኔታ ጋር ማስማማት።


ሌላው ቁልፍ ተግባር በገጽ-ለገጽ፣ በOnline ወይም በሁለቱም ዘዴዎች ወቅታዊ የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳን መሰረት በማድረግ የስታትስቲክስ
አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን፣ የመማማርን እና ዕውቀት የማጋራት ባህልን ለማሳደግ የተለያዩ የስታቲስቲክስ ስልጠና ፕሮግራሞችን ማስተባበር
ነው። የስልጠና ኮርሶቹ ከonboarding/ induction (አዳዲስ ተቋሙን ለተቀላቀሉት የሚሰጥ) ጨምሮ በስታቲስቲክስ መረጃ ከዲዛይን
እስከ ስርጭት (D to D) ለሚከናወኑ ስራዎች የሚያስፈልጉ ቴክኒኮችን፣ ሜቴዶሎጂዎችን እና የተለያዩ የሶፍትዌር ክህሎቶችን፣ የዳታ ሳይንስ
እና ዘመናዊ አሰራርን፣ እንዲሁም የአመራርነት፣ የተግባቦት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚኖረን መስተጋብር ላይ የሚያስፈልጉ ልል ክህሎት
(Soft Skill) ያካትታሉ። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በስታቲስቲክስ ምርምር እና ስልጠና የልህቀት ማዕከል ለመመስረት አልሟል።


መሪ ሥራ አስፈፃሚው ተግባሩን እና ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት በሁለት ዴስኮች ተደራጅቷል። እነዚህም፡-

ውጤቶች