የስታቲስቲካል መረጃ ስርጭት እና ተደራሽነት
መግቢያ
የስታቲስቲክስ መረጃ ስርጭት እና ተደራሽነት መሪ ሥራ አስፈጻሚ (CEO) በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት (ESS) ከናሙና ጥናቶች፣ ከቆጠራዎች እና ከአስተዳደራዊ መረጃ ምንጮች የሚመነጩ መደበኛ የስታቲስቲክስ መረጃዎች ለተጠቃሚዎች በወቅቱ ይፋ እንዲሆኑ፣ በቀላሉ እንዲደርሱ እና ለአጠቃቀም ቀላል እንዲሆኑ ያደርጋል። በመሆኑም የስታቲስቲክስ ግልጽነትን በማበረታታት በመንግስት፣ በልማት አጋሮች እና በህዝብ ዘንድ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲወሰን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ዋና ዓላማ
ከፍተኛ ጥራት ያለው ስታቲስቲካዊ መረጃ በጊዜው፣ በፍትሃዊነት፣ ለተለያዩ ተጠቃሚዎች በቀላሉ የሚደርስ፣ ግልጽ እና
የሚጠቀሙበት እንዲሆን ማረጋገጥ።
ዋና ዋና ተግባራት
- • ከናሙና ጥናቶች፣ ከቆጠራዎች እና ከአስተዳደራዊ ምንጮች የሚመነጩ መረጃዎችን በጊዜያቸው ይፋ ማድረግ፣
- • STATBANK፣ ሌሎች የማይክሮ ዳታ ስርጭት ፕላትፎርሞችን እንዲሁም የተቋሙን የመረጃ ማከማቻ ዳታቤዝ (ቋት) ማደራጀትና ማስተዳደር፣
- • ይፋ ለሚደረጉ መረጃዎች (Data Anonymization) ማከናወን፣ በአመቺ ፎርማት መቅረጽ፣ ገላጭ ሰነድ (ሜታዳታ) ማዘጋጀት፣ እና የማማከር አገልግሎት መስጠት፣
- • ይፋ የተደረጉ የጥናት ውጤቶች ሪፖርቶችን በቀላሉ ለመረዳት የሚያግዙ (Visualizations) ውጤቶችን በዳሽቦርዶች ማቅረብ እና ተጠቃሚን ባማከለ ትንተና (Trend Analysis) መስራት፣
- • ተቋማዊ የስታቲስቲክስ መረጃ ማዕከል (ቋት) እና የእውቀት አስተዳደር ስርአቶችን ማስተዳደር፣
ዋና ውጤቶች
- • ለሁሉም መረጃ ተጠቃሚዎች የሚሆኑ መረጃዎችን (PUFs) ደህንነቱ በተረጋገጠ መዳረሻ ማቅረብ፣
- • የስታቲስቲካል ሪፖርቶችን እና ህትመቶችን በጊዜያቸው ከአንድ ማዕከል ማሰራጨት፣
- • የመረጃ ማሰራጫ ፖርታሎችን (STATBANK, IMIS,..) እና የማዕከል ዳታቤዞችን መጠበቅ እና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ማሻሻል፣
- • ይፋ የተደረጉ የጥናት ውጤቶችን በቀላሉ ለመረዳት በሚያግዙ በዳታ ቪዙዋላይዜሽን (ግራፎች፣ ዳሽቦርዶች፣ ኢንፎግራፊክስ) ማቅረብ፣
ፋይዳ
- • የታመነ፣ በጊዜው የሚደርስ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው የስታቲስቲክስ መረጃ መዳረሻነት፣
- • በፖሊሲ ማዘጋጀት፣ እቅድ አውጣጥ እና ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የስታቲስቲክስ መረጃ አጠቃቀም መጨመር፣
- • የአስተዳደራዊ መረጃ እና ናሙና ጥናት መረጃን በመዋሃድ አጠቃቀም ማሻሻል፣