የቫይታል ስታቲስቲክስ የስራ ክፍል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት (ESS) ኮር የሥራ ክፍል ሲሆን ሀገራዊ የቫይታል ስታቲስቲክስ መረጃዎችን የማጠናቀርና የማሰራጨት ሕጋዊ ኃላፊነት ተጥሎበታል። የስራ ክፍሉ እንደ አዲስ የተደራጀው የኢትዮጵያ የሲቪል ምዝገባና ቫይታል ስታቲስቲክስ (CRVS) ሥርዓት በ2004 ዓ.ም በሕግ መደራጀቱን ተከትሎ ነው (በስታቲስቲክስ ሕግ ቁጥር 442/1997 እና በአዋጅ ቁጥር 760/2004)። የስራ ክፍሉ ቀዳሚ ተግባር ከአስተዳደራዊ የሲቪል ምዝገባ የሚገኙ መረጃዎችን ጥራቱ ወደ ጠበቀ በመዝገብ ላይ የተመሠረተ ስታቲስቲካዊ መረጃ በመለወጥ ለተጠቃሚዎች ማቅረብ ነው።


የስራ ክፍሉ ዓላማ በሲቪል ምዝገባ  ላይ የተመሠረቱ  የስታቲስቲክስ መረጃዎችን  ማጠናቀር፣ ማቀነባበር፣ መተንተንና ማሰራጨት ነው። እነዚህ መረጃዎች ለዕቅድ ዝግጅት፣ ለሀብት ክፍፍልና ለፖሊሲ ቀረጻ እንደ ወሳኝ መረጃ ያገለግላሉ።


የቫይታል ስታቲስቲክስ የስራ ክፍል  ተግባራቱን የሚያከናውነው በስሩ በተደራጁት ሶስት ዴስኮች እና  የመረጃ ማቀነባበር ሥራን በሚያግዙት 26 የስታቲስቲክስ  ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አማካኝነት ነው። የስራ ክፍሉ በሚከተሉት ሦስት የቴክኒክ ዴስኮች የተደራጀ ነው፦


የስራ ክፍሉ  የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ፦


በቫይታል ስታቲስቲክስ የስራ ክፍል የሚዘጋጁ የስታቲስቲክስ ሪፖርቶች  ፦