የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጫ ጥናት የመስክ ስራ ተገመገመ

ሐምሌ 3/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እያከናወነ የሚገኝው የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጫ ጥናት የመስክ ስራ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተገመገመ፡፡በግምገማው መድረክ የ20 የመስክ ስራው አስተባባሪዎች ሪፖርትና የማህበራዊና አካቶ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጥሩዘር ተናኜ ማጠቃለያ ሪፖርት ቀረቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

በግምገማው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የተቋሙ የስነ ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተሻገር እስከ አሁን የተሰሩ ስራዎች በጥሩ ሁኔታ የተከናወኑ መሆኑን አንስተው ቀሪ ስራዎችን በታቀደዉ ጊዜ ለማጠናቀቅ በበለጠ ትጋት መስራት እንደሚያስፈልግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

a3a7602
a3a7661
a3a7630
a3a7615