የሀገር አቀፍ የሥራ ሥምሪት እና የፍልሰት ስታቲስቲክስ ጥናት ውጤት ይፋ ተደረገ

ነሐሴ 30/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከመስከረም 2017ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ስያካሂድ የቆየው የብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት አካል የሆነውን የሥራ ሥምሪትና የፍልሰት ስታቲስቲክስ ጥናት ውጤት ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡

በመረጃ ስርጭት ወርክሾፕ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ባለፉት የመካከለኛ ዘመን (2016-2018) በስታቲስቲክስ የልማት እቅድ ከታቀዱት ዋና ዋና የመረጃ ልማት ውስጥ በየወሩ ከሚሰራጨው የገበያ ዋጋ መረጃ በተጨማሪ የስነ ህዝብ እና ጤና ጥናት ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች ይፋ መደረጉን አንስተው በዛሬው ዕለት የስራ ስምሪት እና የፍልሰት መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች ይፋ እንደሚደረግ ገልጸው፤ ይፋ የሚደረገው ሀገር አቀፍ የሥራ ሥምሪትና ፍልሰት መረጃዎች መንግስታዊ ወቅታዊ የሆነ የሥራ ሥምሪት እና የፍልሰት ፖሊስና ዕቅድ ለማዘጋጀት እንዲሁም ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው አስረድተው ፣ተቋሙ በዚህ ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን መንግስት ለስታቲስቲክስ ልማት በሰጠው ትኩረት ሀብት እና ሎጂስቲክስ እንዲሟላ በማድረግ፣የፕላን እና ልማት ፣የገንዘብ ሚኒስቴር፣የተለያዩ መንግስት ሴክተሮች ፣የክልሎችና የከተሞች መስተዳድር አካላት ፣ የሙያ ማህበራት እና የጥናት ኢንስቲትዩቶች፣ ዩንቨርስቲዎች ፣የሀገራችን ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ፣ የአለም የሥራ ድርጅት(ILO) እና የአለም ስደተኞች ድርጅት(IOM)) ለተደረገው የቴክኒክ ፤ፋይናንስ ድጋፍና ትብብር እንዲሁም ለዚህ ቀን እስከምንደርስ ድረስ ሙያው የሚጠይቀውን ዲሲፕሊን ጠብቀው ፤ሥራውን በላቀ ደረጃ እንዲፈጸም ላደረጉት ከተቋሙ ከፍተኛ አመራር እስከ መረጃ ሰብሳቢዎች ድረስ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መላው የአገልግሎቱ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በመረጃ ስርጭት ወርክሾፕ ላይ ተገኘተው የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በረከት ፍስሃጽዮን ኢትዮጵያ የስታቲስቲክስ መረጃ ሉአላዊነቷን ለማረገጋጥ የሚያስችላትን ክ2016-2018 ዓ.ም የቆየ ሶስት ዓመታት የስታቲስቲክስ ልማት ስትራቴጂ ቀርጻ ተግባራዊ ማድረግ እንደተቻለ ገልጽው ዛሬ ይፋ የተደረጉት የሥምሪት እና የፍልሰት መረጃዎች ፤ለቀጣይ አመታት በሀገራችን የሥራ ሥምሪትና ፍልሰትን በሚመለከት ለሚዘጋጁት ፖሊስ፤ ስትራቴጂና ዕቅድ ቀረጻ እንደ ዋናኛ ግብዓት እንደሚያገለግል በማስረዳት የጥናቱ መስክ ስራና ሪፖርት ዝግጅት በስኬት ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ በትጋት ለሰሩት፣ ለተቋሙ ከፍተኛ አመረራሮች ፣ለመላው ሰራተኞች፣ድጋፍና ትብብር ላደረጉ ለፌዴራል፣ ለክልል የመንግስት አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአለም አቀፍ የስራ ድርጅት (International lobour Organization/ILO) የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩንቡላ ነዳበ ( Mr. Khumbula Ndaba) ድርጅታቸው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክ አገልግሎት ወቅታዊና ጥራቱ የተሟላ የሰው ሀይል ስምሪት መረጃ ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የመረጃው ተጠቃሚዎች መረጃውን ከዛሬ ጅምሮ ከተቋሙ ድረ-ገፅ www.ess.gov.et. ላይ ገብተው ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

a3a4906 1
a3a4887 1
a3a4988 1
a3a4924 1
a3a5095
a3a5031 1
a3a5039 1
a3a5066 1
a3a4936 1
a3a5166
a3a5142 1

News