ዓመታዊ የግብርና ጥናት የመስክ ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ

መስከረም 15/2019ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የመኽር ወቅት የግብርና ናሙና ጥናት የመስክ ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ቡድን በአዳማ ቅ/ጽ/ቤት ስር በሚገኙት ኢተያ፣ ቆቃ እና ወንጂ አካባቢ ባሉት የቆጠራ ቦታዎች ባደረገው የመስክ ጉብኝት ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በ27ቱ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ስር በሚገኙት በገጠር 3150 እና በከተማ 1480 የቆጠራ ቦታዎች ስራው በተመሳሳይ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የግብርና ናሙና ጥናት በየዓመቱ ሀገራችን የግብርና ሴክተር ምርትና ምርታማነት ዕድገትን፤ የእንስሳት ሀብት ብዛትና አስተዋጽኦ እንዲሁም ሌሎች ከግብርና ሥራ ጋር የተያያዙ የስታቲስቲክስ መረጃዎችን ለማስገኘት የሚከናወን የተቋሙ ቁልፍ ተግባር ነው፡፡

a3a3854
a3a3578
a3a3551
a3a3510
a3a3709
a3a3717
a3a3590
a3a3873

News