አዲስ አበባ መስከረም 26/1/2019 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለአምስተኛ ዙር ያካሄደውን የስነ_ ህዝብና ጤና ጥናት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የመጀመሪያ ውጤት ይፋ አደረገ።
በወርክሾፑ መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስነ_ ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተሻገር ወርክሾፑ በክልል ደረጃ የመጀመሪያ እንደሆነ አንስተው በወርክሾፑ የክልሉን የጥናቱ የመጀመሪያ ውጤት ሪፖርት ይፋ የሚደረግበት ብቻ ሳይሆን ከጥናቱ የተገኙትን መረጃዎች በቀጣይ በክልሉ በሚካሄዱ የማህበራዊ ዘርፍ የልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል እንዳለባቸው በመወያየት የጋራ ግንዛቤ የሚፈጠርበት መድረክ መሆኑን በማስረዳት ለስራው ስኬት በክልሉ በየደረጃው የሚገኙት የአስተደዳር አካላትና ህዝቡ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ወርክሾፑን የአዲስ አበባ የስታቲስቲክ ቅ/ጽ/ቤት ያዘጋጃው ሲሆን ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎችና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች በመድረኩ የተሳተፉ ሲሆን በክልሉ ላይ ያተኮሩ የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች ገለጻ ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል።














