በተቋሙ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተደረገ

የካቲት 28/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፤

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት  የ2017ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደረገ።

የስራ አፈጻጸሙን ግምገማ መድረክ በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ባለፉት ስድስት ወራት እንደ ተቋም ታላላቅ ሀገር አቀፍ  ጥናቶች እና ቆጠራ በከፍተኛ ትጋትና ትበብር ተጅምረው በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው በዛሬው መድረክ ላለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት የነበሩንን ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶች ላይ በመወያየት በቀጣይ ቀሪ ወራት ለሚከናወኑ ተግባራት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ለመሰብሰብ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን በማስረዳት ውይይቱን አስጀምረዋል ።

የ2017ዓ.ም ባለፉት ስድስት ወራት የተቋሙን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በአቶ ሁሴን አጎናፍር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የግማሽ ዓመቱ የተቋሙ አጠቃላይ አፈጻጻም 83.4% መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል። ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች የሁሉም የተቋሙ ባለሞያዎች ጥረት እና ትጋት የተመዘገቡ እንደሆነ በመጥቀስ ምስጋና ያቀረቡት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ በቀጣይ ቀሪ ስድስት ወራት እየተከናወኑ የሚገኙትን ጥናቶች እና ቆጠራዎች እስካሁን ካሳካነው በተሻለ ትጋት ማጠናቀቅ እንዲሁም በተቋሙ የተጀመሩ የሪፎርም ተግባራት በተሟላ መልኩ በማጠናቀቅ ወደ ስራ ማስገባት የቀጣይ ጊዜ የትኩረት ተግባራት እንደሆኑ የስራ አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

001 1
002
004
006
007
008