ጥር 17/2018 ዓ.ም አዳማ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በመካከለኛው ዘመን (2016 – 2018 ዓ.ም) የስታቲስቲክስ ልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ ክንውን ላይ ከተወካዮች የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት አካሄደ። በመድረኩ ተገኝተው ስልጠናውን ያስጀመሩት የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጀ ተቋሙ ላለፉት ስድስት አስርት አመታት ለሀገሪቱ ልማት ዕቅድ ፖሊሲና ስትራቴጂ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉትን መረጃዎች በማቅረብ በየዘመኑ በሀገራችን ለተመዘገቡ […]