
ግንቦት 26/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ የስምንት ወራት መስክ ስራ አፈፃፀም በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ተገመገመ።

በመላ ሀገራችን እያተከናወነ የሚገኘው ሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ ያለፋት ስምንት ወራት መስክ ስራ አፈፃፀም ሪፖርት የተቋሙ ከፍተኛአመራርና የቆጠራው ቴክኒካል ኮሚቴ አባላት በተሳተፋበት መድረክ ቀርቦ በተደረገው ግምገማ የባለፋት ስምንት ወራት የመስክ ስራ አፈፃፀም በታቀደው መሠረት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ የተገመገመ ሲሆን በቀጣይ ወራት የሚከናወኑ ቀሪ የመስክ ተግባራት በተቀመጠላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ የስራ መመሪያ ተሰጥቶ የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።
