ነሐሴ 23/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የቀድሞ የተቋሙ ሰራተኞች የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ስራ እንዲሳተፉ ጥሪ ተደረገላቸው።

ለቀድሞ የተቋሙ ሰራተኞች እንኳን በሰላም ወደቤታችሁ መጣችሁ ያሉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በተቋሙ ቆይታችሁ ያፈራችሁትን ዕውቀት፣ ክህሎትና ልምድ አሁን ላሉት ወጣት የስታቲስቲክስ ባለሙያዎች እንድታካፍሉና ለዚህ ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ስኬት የድርሻችሁን እንድታበረክቱ ታስቦ የተደረገ ቤተሰባዊ ጥሪ እንደሆነ አስረድተው፤ ይህ ተግባር ነባሩን የተቋሙ ዕውቀት ለአዲሱ ትውልድ የማካፈል የሰው ሀይል አቅም ግንባታ ስትራቴጂ አንድ አካል ተደርጎ እየተሰራበት የሚገኝ ቁልፍ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።

የተቋሙ የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው የተቋሙ አሁናዊ ሁኔታ ላይ ገለፃ አቅርበው ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል።

የቀድሞ የተቋሙ የስራ ባልደረቦችም ተቋሙ አሁን በደረሰበት ደረጃ ደስተኛ መሆናቸውንና አሁንም ሀገራችን ማገልገል እንድንችልና ልምዳችንን እንድናካፍል ዕድል ስለተሰጠን እናመሰግናለን ሲሉ ገልፀዋል።
