የሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ የመስክ ስራ አፈፃፀም ሶስተኛ የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም የሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ የመስክ ስራ አሁናዊ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ ለሶስተኛ ጊዜ በአዳማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ተገኝተው ውይይቱን ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክቴር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋማችን ለዘመናት ያካበተውን ልምድ፣ የሰው ሀይልና ጥቂት ሀብት ይዘን የተቀናጀ አመራር በመስጠት ውጤታማ እንደምንሆን በከፍተኛ ተስፋ የተጀመረ የቆጠራው የመስክ ስራ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ በትጋት ለሰሩት ሰራተኞች በመሉ ምስጋና በማቅረብ መድረኩን ያስጀመሩ ሲሆን በመድረኩ የመስክ ስራው አሁናዊ ሁኔታ በመገምገም በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት የተሻለ ዝግጅት ለማድረግ ግንዛቤ የሚፈጠርበት መድረክ መሆኑን አስረድተዋል። በመድረኩ የሁሉም ክላስተር የመስክ ስራ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።