የቤተሰብ በጀት እና የሌበር ስታቲስቲክስ መሪ ሥራ አስፈፃሚ
ለአገራዊ ደህንነት ክትትል፣ ለድህነትና የስራ አጥነትን ለመቀነስ ስትራቴጂዎች እና በማስረጃ ላይ ለተመሰረተ የፖሊሲ እቅድ መሠረት የሚሆኑ ጥራት ያላቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን ማቅረብ።
ዋና ዓላማ
የቤተሰብ በጀትና የስራ ስምሪት ስታቲስቲክስ የተቋቋመው የህዝቡን የኑሮ ደረጃ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለመለካት ነው። ይህ የሥራ ክፍል ዋና ዓላማ በተለይ የሥራ ገበያ፣ የቤተሰብ ፍጆታና ወጪ፣ የድህነት ቁጥጥር እና የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ አመላካቾችን በማዘጋጀት፣ የቤተሰብን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በትክክል በመሰብሰብ፣ መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት ለልማት አገራዊ መፍትሄዎችን ለመንደፍ፣ ለፖሊሲ ውሳኔ፣ ለልማት እቅድ እና ለማህበራዊና ኢኮኖሚ አስተዳደርና ልማት የሚጠቅሙ ትክክለኛና ዘመናዊ መረጃዎችን በማመንጨት የሀገር የስታቲስቲካዊ ልዕልና ማጠናከር ነው።
ዋና ተግባራት
- • የስራ ስምሪት ጥናቶችን እና የቤተሰብ በጀት ጥናቶችን ማካሄድ
- • የህዝብ የኑሮ ሁኔታ ክትትል መረጃዎችን ማቅረብ
- • የቤተሰብ በጀትና የፍጆታና ወጪ መረጃ ማሰባሰብና መተንተን
- • የህፃናት ሥራ ስምሪት መረጃ ማመንጨትና የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ስርጭት፣ መንስኤዎችና ተጽኖዎች ላይ ጥናት ማካሄድ።
- • መስፈርቶችን ማዘጋጀት፦ በዋናነት የድህነት ምጣኔን እና የሥራ ስምሪት ደረጃዎችን አመላካቾችን ማስላት።
- • የጥራት ቁጥጥር፦ መረጃዎች ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የጠበቁ እና አገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘቡ መሆናቸውን ማረጋገጥ።
- • ለፖሊሲ እና ለልማት እቅድ የሚያገለግሉ መለኪያዎችን ማዘጋጀት
የሚመነጩ ስታቲስቲካዊ ጥናቶችና ዋና ዋና የጥናቶች ውጤቶች
- • ብሔራዊ የስራ ስምሪት ጥናት: የስራ ተሳትፎ ምጣኔ፣ የስራ እአጥነት፣፣ የስራ ሰዓት፣ ከቅጥር ስራ የተገኝ ገቢ
- • የከተማ ተከታታየ የስራ ስምሪት ጥናት፡ የስራ ተሳትፎ ምጣኔ፣ የስራ እአጥነት፣፣ የስራ ሰዓት፣ ከቅጥር ስራ የተገኝ ገቢ በከተማ
- • የቤተሰብ ፍጆታና ወጪ ጥናት: ፍጆታና ወጪን የሚለካና የምግብ ዋስትናን መተንተን
- • የቤተሰብ የኑሮ ደረጃ ክትትል: የቤተሰብ ደህንነት ቁጥጥር ፣ እኩልነት፣ ማህበራዊ የመሰረታዊ አገልግሎቶች (ጤና፣ ትምህርት፣ ውሃ) ተደራሽነትን ተጠቃሚነት የሚዳሰስና መገምገም
- • የህፃናት ሥራ ጥናት : የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ፣የወደፊት የሕጻናት በኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለመጠበቅና አደገኛ ሥራዎችን የሚለካና አደጋዎችን እና ስርጭቶችን መለየት
- • ለፖሊሲ እና ለውሳኔ የሚያገለግሉ ማስተናገድ ውጤቶች