የስታቲስቲክስ መረጃ ቅንጅት፣ ስታንዳርድ እና ጥራት
የስታቲስቲክስ መረጃ ቅንጅት፣ ስታንዳርድና ጥራት መሪ ሥራ አስፈጻሚ በሁለት ዴስኮች ማለትም የስታቲስቲክስ መረጃ ጥራትና ስታንዳርድ ዴስክ እና የፕሮግራም ማረጋገጫ /Program Verification Desk/ የተዋቀረ እና የስታቲስቲክስ፣ የጂ.አይ.ኤስ እና የኮምፒውተር ፕሮግራመር ባለሙያዎች የተዋቀረ ክፍል ነው። ይህ መሪ ሥራ አስፈፃሚ የስታቲስቲክስ ስታንዳርድን በመቅረጽ፣ የስታቲስቲክስ መረጃ አቅርቦት እና ጥራትና ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራትን ይመራል፣ ያስተባብራል። ይህ የስራ ክፍል ከናሙና ጥናቶች፣ ከቆጠራዎች እንዲሁም ከአስተዳደራዊ መዝገቦች የሚመነጭ የስታቲስቲክረስ መረጃ በተቀናጀ ሁኔታ ጥራቱን እና ወቅቱን የጠበቀ እንዲሆን፤ በስታቲስቲክስ ተግባራት ላይ የሚተገበሩ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ጥራት የማረጋገጥ ተግባራትን ይመራል፣ ያስተባብራል። በተጨማሪም ተቋሙ ገለልተኛ አረጋጋጭ በመሆን በተለያዩ ዘርፎች የሚተገበሩ ውጤት ተኮር ፕሮግራሞችን (PforR) የማረጋገጥ ወሳኝ ኃላፊነት ይወጣል። ስለሆነም ጥራት እና ደረጃቸውን የጠበቁ የማረጋገጫ ሪፖርቶችን ለማቅረብ በጋራ የተስማሙባቸውን ደረጃቸውን የጠበቁ የማረጋገጫ ሥነ-ዘዴዎችን በመጠቀም በመረጃ ላይ የተመሠረተ ልማት እንዲፋጠን እና በውጤት ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ፍሰት እንዲቀላጠፍ ተቋሙ ኃላፊነቱን እንዲዎጣ በከፍተኛ ትጋት እየሰራ ይገኛል።
ዋና ግብ
የስታቲስቲክስ ደረጃዎችን በማቀናጀት እና በውጤት ላይ ለተመሰረቱ ፕሮግራሞች ላይ ገለልተኛ አረጋጋጭ በመሆን ቁልፍ አገልግሎት በመስጠት የስታቲስቲክስ ልህቀትን እና ተዓማኒነትን በሥርዓት ለመገንባት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት፤
ዋና ዋና ዓላማዎች
- • የስታቲስቲክስ መረጃ ጥራት ግምገማ ማዕቀፍ (EDQAF) እንዲዘጋጅ፣ እንዲተገበርና ክትትል እንዲደረግበት ማስተባበር፤
- • ዓለም አቀፍ የስታቲስቲክስ ፅንሰ-ሐሳቦችና ምደባዎች እንዲዘጋጁ ማስተባበርና ሜታዳታ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ፤
- • መረጃ መሰብሰቢያና ማቀነባበሪያ የሚውሉ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች እና የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ጥራትና ስታንዳርድ እንዲጠበቅ መምራት
- • የፕሮግራሞች ውጤት ማረጋገጫ (PforR) ስራዎችን መምራትና ከገንዘብ ፍሰት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ውጤቶች (DLIs) ማረጋገጥ፤
ዋና ዋና ተግባራት
- • የኢትዮጵያ የስታቲስቲክስ መረጃ ጥራት ቁጥጥር ማዕቀፍ (EDQAF) በሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታና በዓለም አቀፍ መስፈርት እንዲዘጋጅ፣ እንዲተገበርና ክትትል እንዲደረግበት ማስተባበር፤ እንዲሁም የመረጃ ጥራት ግምገማ ሪፖርት (Quality Report) እንዲዘጋጅ ማድረግ፤
- • ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን መሠረት ያደረጉ የስታቲስቲክስ ፅንሰ-ሐሳቦች፣ ፍቺዎች፣ ኮዶችና ምደባዎች ዝግጅትን ማስተባበር፤ እንዲሁም የተደራጀና የተቀናጀ ሜታዳታ (Metadata) እንዲዘጋጅና ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ፣
- • የስታቲስቲክስ ናሙና ጥናቶች እና ቆጠራዎች የሜቶዶሎጂዎችን ጥራት እና ስታንዳርን ማረጋገጥ፤ የጥናቶች እና ቆጠራዎች የመጠይቅ ዝግጅትን፣ የመረጃ መሰብሰቢ፣ ማቀነባበሪ እና ትንተና ዘዴዎችን ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
- • የፕሮግራሞች ውጤት ማረጋገጫ (Program for Results (PforR) Verification) ስራዎችን መምራት፤ የማረጋገጫ መመሪያዎችን (Verification Manual) ማዘጋጀትና የማረጋገጫ ውጤት ሪፖርቶችን ለባለድርሻ አካላት ማቅረብ፣
- • በሁሉም ስራ አስፈጻሚዎች ለሚበለጽጉ የናሙና እና የቆጠራ መረጃዎች ማሰባሰቢያና ማቀናበር የኮምፒውተር ፕሮገራሞችን እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስታንዳርዳይዝ በማድረግ ጥራታቸውን እንዲጋገጡ የክትትሉነና ቁጥጥሩን ሂደት መምራትና ማስተባበር፤