መስከረም 19/2019ዓ.ም አዲስ አበባ፣
ኢትዮጵያኖች እና የሌላ አለም ዜጎች ስለ ኢትዮጵያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማወቅ የሚያግዝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብራንዲግ ግንዛቤ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል ስልጠና ከተቋሙ 14 ቅ/ጽ/ቤት ለተውጣጡት ከፍተኛ ባለሙያዎች በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የጥናቱ ዓላማ ከጥናቱ የሚገኙትን መረጃ እንደመነሻ በመውሰድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብራንዲግ መሻሻል ያለመ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ጥናቱን የኢትዮጵያ ስታስቲስቲክስ አገልግሎት፣ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ፖሊሲ ጥናት ኢንስትቲዩት እና የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ጥናት ኢንስትቲዩት በጋራ ያከናውናሉ፡፡


