መስከረም 27/01/2019 ዓ.ም አዳማ
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከሚያቀርባቸው የስታቲስቲክስ መረጃዎች አንዱ የሆነው ዓመታዊ የስታቲስቲክስ (Annual Statistical Abstract )መጽሔት ይዘት ለማሻሻል የሚያስችል አውደጥናት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ተገኝተው አውደጥናቱን ያስጀመሩት የማህበራዊና አካቶ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጥሩ ዘር ተናኜ ተቋሙ ባለፉት ዓመታት ሲያቀርብ የቆየውን ዓመታዊ የስታቲስቲክስ መጽሔት ይዘት አሁናዊ የመረጃ ተጠቃሚዎችን ፍላጎት በሚመጥን መልኩ ማሻሻልና ማዘመን በማስፈለጉ አውደጥናቱ መዘጋጀቱን ገልፀው፣ ተሳታፊዎች በአውደ ጥናቱ ሊከናዋኑ የታሰቡት ተግባራት እንዲሳኩ በትጋትና በትኩረት እንዲሰሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
በአውደ ጥናቱ ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ከተለያዩ የስራ ክፍል የተወጣጡ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን ዓመታዊ የስታቲስቲክስ (Annual Statistical Abstract ) መጽሔት ይዘት ስለሚሻሻልበት፣ የዝግጅት ጊዜ ፣ ከመረጃ ምንጮች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እንደሚከናወኑ ተጠቅሷል ።







