የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአምስተኛ ዙር ስነ_ህዝብና ጤና ጥናት የመጀመሪያ ውጤት ይፋ ተደረገ፤

አዲስ አበባ መስከረም 28/1/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለአምስተኛ ዙር ያካሄደውን የስነ_ህዝብና ጤና ጥናት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ውጤት ይፋ አደረገ።

በወርክሾፑ መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስነ_ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተሻገር ወርክሾፑ  የከተማ አስተዳደሩ የጥናቱ የመጀመሪያ ውጤት ሪፖርት ይፋ የሚደረግበት ብቻ ሳይሆን ከጥናቱ የተገኙትን መረጃዎች በቀጣይ በከተማው በሚካሄዱ የማህበራዊ ዘርፍ የልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል እንዳለባቸው በመወያየት የጋራ ግንዛቤ የሚፈጠርበት መድረክ መሆኑን በማስረዳት ለስራው ስኬት በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙት የአስተደዳር አካላትና ህዝቡ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ ከጥናቱ የተገኙ መረጃዎች የከተማ ጤና ዘርፍ ለማሻሻል እና ለማዘመን ለሚዘጋጁ ዕቅድ ክትትልና ግምገማ እንደ ዋና ግብአት እንደሚጠቀሙበት አንስተው ተቋሙ ጥናቱን በስኬት በማጠናቀቅ የመረጃ ስርጭት ወርክሾፕ  በማዘጋጀቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወርክሾፑን የአዲስ አበባ የስታቲስቲክ ቅ/ጽ/ቤት ያዘጋጃው ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ከተለያዩ ቢሮዎች የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች በመድረኩ የተሳተፉ ሲሆን በከተማው ላይ ያተኮሩ የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች ገለጻ ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

a3a4268 1
a3a4245
a3a4320 1
a3a4311
a3a4461 1
a3a4471
a3a4490
a3a4494
a3a4488
a3a4432
a3a4455 1
a3a4481
a3a4507

News