ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
ከመላ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የ10ኛው የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ኮሚሽን ዓመታዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የሚገኘውን የሳይንስ ሙዚየም ጎበኙ፡፡ ጉብኘቱን ላዘጋጀው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበው በሳይንስ ሙዚየሙ ያዩት ቁምነገር ለሀገራቸው የሚመኙት እና በጣም ጠቃሚ እንደነበረ አንስተው በጉብኘቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡











