10ኛው የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ኮሚሽን ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

​   ጥቅምት 11/ 2019 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

10ኛው የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ኮሚሽን (StatCom-Africa) ጉባኤ በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ዋና መስሪያ ቤት“የመረጃን እሴት በአፍሪካ ማሳደግ፡ ኦፊሴላዊ ስታቲስቲክስን የእውነተኛዋን አፍሪካ ትክክለኛ መስታወት ማድረግ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ታዬ አጽቀሥላሴ የመረጃ እውነተኛ እሴት በመሰብሰብ ላይ ብቻ ሳይሆን፤ የመረጃውን እውነትነት ወደተረጋገጠ፣ የተግባር መመሪያ ወደሚሆን እና የሕዝቦቻችንን እውነተኛ ህይወት የሚለውጥና የአህጉራችንን እድገት ወደሚያመጣ እውቀት መለወጥ ላይ ነው ሲሉ ገልጸው የአፍሪካ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ለብሔራዊ የስታቲስቲክስ ቢሮዎች(NSOs)  ገለልተኝነት እና ቴክኒካዊ አቅም ማጠናከሪያ የሚሆን የሀገር ውስጥ በጀት እንዲመድቡና የመረጃ ግላዊነትን ለማረጋገጥ፣ የህዝብ እምነትን ለመገንባት እና የአህጉሪቱን ስትራቴጂካዊ የመረጃ ሀብቶች ለመጠበቅ ጠንካራ የሕግና የቁጥጥር ማዕቀፎች እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርበው ኢትዮጵያ በመረጃ ላይ የተመሰረተ አመራር እና ተቋማዊ እምነትን በመገንባት የለውጥ ጉዞዋን ለማፋጠን ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ሥራ አስፈፃሚ ሴክሬታሪ ክቡር አቶ ክላቨር ጋቴቴ በአዲስ አበባ በተካሄደው 10ኛው የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ኮሚሽን (StatCom-Africa) ጉባኤ መክፈቻ ላይ ያደረጉት ንግግር የስታቲስቲክስ ሥርዓቶች የአፍሪካን ወቅታዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ የመደበኛ ያልሆነው የኢኮኖሚ ዘርፍ እውነታዎችን እና የሕዝብ ቁጥር እንቅስቃሴዎችን በትክክል የሚያንፀባርቁ  መሆን አለባቸው ሲሉ ገልጸው  የአፍርካ ሀገራት የመረጃ አሰባሰብ ፍጥነትን እና ስፋትን ለማሻሻል ብሔራዊ የስታቲስቲክስ ቢሮዎች (NSOs) ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን፣ ቢግ ዳታን (Big Data)፣ አስተዳደራዊ የመረጃ ሥርዓቶችን እና የጂኦስፓሻል መረጃ ሥርዓቶችን (GIS) በመተግበር ሥርዓታቸውን እንዲያዘምኑ አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሶስት ዓመታት ተቋማዊ አቅምና አደረጃጀት ግንባታ፣ የስታቲስቲክስ ህጋዊ ማዕቀፍ መሻሻል፣ የመረጃ አቅርቦትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥተው በሰራቸው ስራዎች የሚጨበጥ ውጤት መመዝገብ መቻሉን አንስተው በቀጣይም ተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን የማረጋገጥ ተግባራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ አስረድተው በተቋማዊ  ግንባታ ጥረታችን ውጤታማ እንዲሆን ድጋፍ ላደረጉት ለመንግስት፣ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ አጋር ተቋማትና ባላድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። 

ጉባኤው የስታቲስቲክስ አቅምን ማጠናከር፣ የሕዝብና ቤት ቆጠራ መስፈርቶችን ማቀናጀት እና በአፍሪካ በመረጃ ላይ የተመሰረተ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የዘርፈ-ብዙ አጋርነቶችን ማጠናከር ላይ ያተኮሩ የጎንዮሽ መርሃ ግብሮችን እና ቴክኒካዊ ውይይቶችን እንደሚካሄዱ ለማወቅ ተችሏል።

በጉባኤው ላይከአህጉሩ የተወጣጡ የስታቲስቲክ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ተወካዮች፣ የስታቲስቲክስ ባለሙያዎች፣ የፖሊሲ ተንታኞች እና ዓለም አቀፍ አጋሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

1
2
3
4 1
5
6
7
8
9
10
11

News