19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን! በሚል መሪ ቃል ታስቦ ዋለ።

ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ ነፃነት፣ ክብርና የብዝኃነታችንን ውበት የሚወክል የጋራ ኩራታችን ነው።
በሰንደቃችን ስር ልዩነታችንን በማክበር፣ አንድነታችንን በማጠናከር እና የጋራ የሆኑ ሀገራዊ እሴታችንን በማሳደግ ለሰላም፣ ለአብሮነትና በአንድነት መቆም ይጠበቅብናል።
ሰንደቅ ዓላማችንን ማክበር የሀገራችንን ክብር ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ለሰላም፣ ለመከባበር፣ ለመተባበር እና ለጋራ ዕድገት ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር ማሳየት ነው።
ልዩነታችንን እንደ ጥንካሬ፣ ብዝኃነታችንን እንደ ውበት በመቀበል፣ ለትውልድ የተሻለች፣ በሰላም የታነጸችና በአንድነት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሁላችንም ሚና ወሳኝ ነው።
ሰንደቃችን የሀገራዊ ኩራታችን፣ የአንድነታችንና የጋራ ማንነታችን ምልክት!
መልካም የሰንደቅ ዓላማ ቀን!

ethiopian flag waving in sunlight

News