ህብረተሰቡ ለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ ቀረበ

ህዳር 4/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ ከጥቅምት 1/2018ዓ.ም ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ እያካሄደ ለሚገኘው የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ በማንኛውም አይነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ቤተሰቦች፣ ተቋማትና ግለሰቦች የቆጠራው መረጃ ሰብሳቢዎች ለሚጠይቋቸው ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ለስራው ስኬታማነት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙት የመንግስት አስተዳደር አካላት ቆጠራው በሀገራችን የኢኮኖሚ ዘርፍ ዕድገት ለመፋጠን ለሚዘገጁ ፖሊስና ዕቅድ ግባኣትነት እንዲሁም ዘርፉ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት እያበረከት የሚገኘውን ድርሻ ለመስላት የሚያስችሉ መረጃዎች የሚገኝበት፤ በመንግስት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ቁልፍ የልማት ተግባር መሆኑ በመረዳት በየአካባቢያቸው ህብረተሰብ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርግ መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ቆጠራው አስመልክቶ ከሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጥሪ አቀረቡ።