
ሐምሌ 25/2017ዓ.ም ሀዋሳ፣
የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ተግባራት ለማከናዋን ወደ ሲዳማ ክልል ለተጓዘው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራር የሲዳማ ክልል የፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አራርሶ ገረመውና በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሀዋሳ ስታቲስቲክስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አሰጋሽ አሰፋ በሀዋሳ አየር ማረፊያ ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከፍተኛ አመራሩ ነገ ሐምሌ 26/2017ዓ.ም በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ዞን ዳራ ወረዳ ናጭሾ ገጠር ቀበሌ በመገኘት የአቅመ ደካማ ቤቶችን ግንባታ መስጀማሪ፣ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መድረግና የችግኝ ተከላ የክረምት የበጎ አድራጎት ተግባራት መርሀ ግብር ላይ ይሳተፋሉ።