ነሐሴ 6/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ሁለተኛ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ለሚሰጥባቸው 13 የተመረጡ ዩኒቨርስቲዎችና እንዲሁም የክልል መንግስት የትምህርት የቴክኒክና ሙያ የስልጠና ማዕከላትና የተቋሙ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ስልጠናውን ለማሳካት የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት ላይ ኦረንቴሽን ተሰጠ።
የስራ ኦረንቴሽኑን በበይነ መረብ የሰጡት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የተሟላ ስልጠና ለመስጠት ከየማዕከላቱ ስለሚጠበቅባቸው ተግባራት የስራ ኦረንቴሽን የሰጡ ሲሆን ይህ ለሀገራችን ትልቅ ፋይዳ ያለው ቆጠራ ስራ እንዲሳካ በስራው የሚሰማራው የሰው ሀይል ወሳኝ መሆኑ ስልጠናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የስልጠና ማዕከላቱ የስራ ኃላፊዎችም በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ተግባር ከተቋሙ ጋር በመስራታቸው ኩራት እንደሚሰማችው ገልፀው ስልጠናውን ለማሳካት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።