በዓመታዊ የስታቲስቲክስ መጽሄት ዝግጅት መነሻ ይዘት ላይ ውይይት ተካሄደ

ሰኔ24/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

aa3a8873

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከተለያዩ ጥናቶችና የአስተዳደር መዛግብት የተገኙትን መረጃዎች በማደረጃትና አስፈላጊውን የጥራት  ደረጃ በመከተል በሚያዘጋጀው ዓመታዊ የስታቲስቲክስ መጽሄት /statistical Abstract/ አካል በሆነው የ2016 ዓ.ም መፅሔት ዝግጅት መነሻ ይዘት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

aa3a8855

የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት የተቋሙ የስነ-ህዝብ እና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተሻገር ተቋሙ ከኢኮኖሚያዊ እና ከማህበራዊ ጥናቶች እንዲሁም ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የአስተዳደር መዛግብትየሚገኙትን መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና በማደራጀት በተለያዩ ፎርማት አዘጋጅቶ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ እያሰራ  እንደሚገኝ አንስተው የስታቲስቲክስ መጽሄት /statistical Abstract/ በርካታ መረጃዎችን በአንድ ፎርማት አካቶ የሚይዝ በመሆኑ፤ ለፖሊሲ፣ ለልማት ዕቅዶች ዝግጅት እና ግምገማና ክትትል እንዲሁም ለልዩ  ልዩ ምርምር ስራዎች እንደአንድ የመረጀ አማራጭ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን በማስረዳት፤ በዓመታዊ መጽሄት የሚካተቱ መረጃዎች  ጥራት እንዲኖራቸው ከቅድመ ዝግጅት ሂደት ጀምሮ የመረጃዎቹን ምንጭ ከሆኑት ባለድርሻ አካላት ጋራ በተዘጋጀው የመጽሄቱ መነሻ  ይዘት ዙሪያ ውይይት በማድረግ የሚገኙትን ተጨማሪ ግብዓቶችን ማካታት አስፈላጊ በመሆኑ የውይይቱ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፀው  ዓመታዊ መጽሄቱ በተቻለ መጠን የመረጃ ምንጭ የሆኑትን ተቋማት የመረጃ ፍላጎት ያማከለና ጥራቱ የተሟላ እንዲሆን ተሳታፊዎች  ያላቸውን ሀሳብ በመስጠት የበኩላቸውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል ።

aa3a8904

በውይይቱ የዓመታዊ የስታቲስቲክስ መጽሄት ዝግጅት መነሻ ይዘት ገለፃ በተቋሙ ማህበራዊ አካቶ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ  ከፍተኛ ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመድረኩ የተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች እንደግብዓት በመውሰድ የውይይት መደረኩ ተጠናቋል።