ተቋማቱ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ

ሐምሌ 24/2017ዓ.ም ለገጣፎ፣

1t8a4592

የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በሸገር ከተማ በለገዳዲ ለገጣፎ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካሄዱ።

1t8a4617

መርሀ ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በሀገራችን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ እስከአሁን ወደ40 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸው አንስተው ይህም በአየር ንብረት ለውጥ፣ በግብርናና በኢኮኖሚው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት የተገኘበት መሆኑን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩን ቀጣይነት በማረጋገጥ ከተረጂነት ለመውጣትና በምግብ ራስን የመቻል እቅድ ለማሳካት ዛሬ የምንተክለው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ሲሉ ገልፀዋል።

1t8a4564

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የሸገር ከተማ የለገዳዲ ለገጣፎ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ም/አስተዳደሪ ወ/ሮ ሰዓዳ እስማኤል በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻር መርሀ ግብር ተግባርን በማስቀጠል ልመናን ታሪክ እናደርጋለን ሲሉ ገልፀዋል።

1t8a4543
1t8a4510
1t8a4695

በዕለቱ ከአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩ በተጨማሪ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት 100 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

1t8a4721
1t8a4723
1t8a4623 2
1t8a4637
1t8a4826 2