ሚያዚያ 4/2017 ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የተሽከርካሪ ስምሪትና የነዳጅ አጠቃቀምን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የሚያስችል የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም ላይ ከዋናው መስሪያ ቤት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።
በተቋሙ ሪፎርም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራባቸው ካሉት ተግባራት አንዱ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ መሆኑን የተቋሙ ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤቢሳ አሰፋ የገለፁ ሲሆን የዛሬው ስልጠናም የተሽከርካሪ ስምሪትን፣ የትራንስፖርትና የነዳጅ አጠቃቀምን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማደረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል። በተጨማሪም ዋና ስራ አስፈፃሚው የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም የተሽከርካሪ ስምሪትን፣ የነዳጅ አጠቃቀምን፣ የተሽከርካሪ እቃ ግዢዎችን፤ ግልፅና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል ስርዓት መሆኑን ከቀረበው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል።
ስልጠናው ከግዢና ንብረት ባለስልጣን በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ከተቋሙ ለተውጣጡ 54 ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።




