የአስተዳደራዊ መረጃ አሰባሰብ፣አያያዝ እና ትንተናን ለማሻሻል የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ሚያዚያ 21/8/2018ዓ.ም አዳማ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የአስተዳደራዊ መረጃ አሰባሰብ ፣ትንተና እና አያያዝ ለማሻሻልና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን የሚያስችል ስልጠና ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ምዕራብና ከሲዳማ ክልል ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የስታቲስቲክስ ሲስተም ልማት እና ሜቶዶሎጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጀሚላ መሃመድ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በመካከለኛ ዘመን የስታቲስቲክስ ልማት ዕቅድ የሀገራችን የፌደራልና የክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች የአስተዳደራዊ መዛግብት መረጃ አሰባሰብ፣አያያዝና ትንተና በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን በማድረግና ጥራቱን በማሻሻል በሂደትም የአስተዳደራዊ መዛግብት መረጃዎች እንደ አንድ የስታቲስቲክስ መረጀ ምንጭ ለመጠቀም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ በማስረዳት፤ ስልጠናው በአስተዳደራዊ መዛግብት መረጃ አሰባሳብ፣አያያዝና ትንተና እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቀቃም ላይ የሚታዩትን የባለሙያ የዕውቀትና ክህሎት ክፍተቶችን በማሻሻል የአስተዳደራዊ መረጃ ጥራትን በማሳደግ ለፖሊሲ፣ እቅድና ስትራቴጅ ቀረፃ እንዲውል የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀው የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናውን በንቃት በመከታተል ያገኙትን ዕውቀትና ልምድ በየተቋማቸው ተግባራዊ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ስልጠናው ከአስተደዳራዊ መዛግብት የሚገኙትን መረጃዎች አሰባሰብ፣ ትንተናና አያያዝ፣ዲጂታል የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች፣የጂኦ-ስፓሻል መረጃ አያያዝ ላይ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ ባለሙያዎች ለሚቀጥለው አንድ ሳምንት እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

1t8a6810
1t8a6814
1t8a6841
1t8a6851
1t8a6854