የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየውን የሁለተኛ ዙር ግብርና ቆጠራ የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ የመረጃ ጥራትን በዕለትተዕለት የመስክ ስራ ተግባራችን በመከታተል ማስተካከልናጥራቱን ማረጋገጥ እንዲሁም የቆጠራው የመረጃ መሰብሰብ ተግባር በታቀደለት ጊዜ ማጠናቀቅ የቀጣይ ቀሪ ወራት የትኩረት ተግባራት መሆናቸውን የስራ መመሪያ በመስጠት የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል፡፡
