ነሐሴ 2/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018ዓ.ም ለሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ በ13 የስልጠና ማዕከላት ከነሐሴ 7/2017ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የአሰልጣኞች ስልጠና ለማስተባበር ከዋናው መስሪያ ቤት ወደ ማዕከላቱ ለተመደቡት 80 ባለሙያዎች የስራ መመሪያ ተሰጠ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ በ2017ዓ.ም በተሰሩት ትላልቅ ሀገራዊ ጥናቶችና ቆጠራ የተገኙትን መልካም ተሞክሮዎች በማስቀጠል እንደክፍተት የታዩትን በማረም ስልጠናው በታቀደው መሰረት ስኬታማ እንዲሆን በከፍተኛ ትጋትና ሀገራዊ ሀላፊነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ስልጠናው ከነሐሴ 7 እስከ 28/2017ዓ.ም በሁሉም ማዕከላት እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።

