መስከረም 2/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018ዓ.ም ለሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ በ54የስልጠና ማዕከላት ከመስከረም 5/2018ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ለማስተባበር ከዋናው መስሪያ ቤት ወደ ማዕከላቱ ለተመደቡት ባለሙያዎች ኦረንቴሽንና የስራ ስምሪት ተሰጠ።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ከ2016 -2018 ዓ.ም በስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራም ታቅደው እየተከናወኑ ያሉ ትላልቅ ስራዎችን ማሳካት የቻልነው ቁርጠኛ በሆነ አመራር፣ በትጋትና ማንኛውም ሁኔታ ሳይገድበን በፍጥነትና በቁርጠኝነት በጋራ በመስራታችን ሲሆን በቀጣይ ለምናካሂደው የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራም ካለፉት የግብርና ቆጠራና ሁለት ጥናቶች መልካም ተሞክሮዎችን በመውሰድና የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻል ካለፈው የተሻለ ስራ ለመስራት ለዚህ ስራ የተሰማሩ ሰራተኞች በሙሉ በትጋትና በዲሲፕሊን እንዲሰሩ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ስልጠናው ከመስከረም 5እስከ 29/2018ዓ.ም በሁሉም ማዕከላት እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
