ለተቋሙ ባለሞያዎች መረጃ የማጥራትና የሪፖርት ዝግጅት ክህሎት ለማሳደግ የሚያግዝ ሥልጠና ተሰጠ

1t8a7881.jpg

ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

ከፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለተወጣጡ ባለሞያዎች “Monetary Welfare and Poverty Measurement” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሥልጠና ተሰጠ።

1t8a7840.jpg

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በተቋሙ እየተካሄደ ላለው ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት (NIHS) የመረጃ ማጥራትና ሪፖርት ዝግጅት ክህሎት ለማሻሻል ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑን ገልጸው፤ በሥልጠናው ያገኛችሁትን ዕውቀት እና ክህሎት ለጥናቱ የመረጃ ማጥራት ሥራ ተግባር ላይ እንድታውሉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈው፤ ለስልጠናው የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ ላደረገው የዓለም ባንክን አመሰግነዋል።

1t8a7828.jpg

ስልጠናው እየተካሄደ የሚገኘው የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት መረጃ የመሰብሰብ ተግባር ከተጠናቀቀ በኋላ በመሆኑ ከጥናቱ የሚገኙትን መረጃዎችን የማጥራትና ለሪፖርት ዝግጅት የሚያስፈልጋቸውን  ክህሎትና ልምድ ያገኙበት ጠቃሚ ስልጠና መሆኑን በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የቤተሰብ፣ በጀትና ሌበር ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፉፋ ቡልቶ ገልጸዋል።

1t8a7813.jpg

ስልጠናው ከነሐሴ 19-23/2017 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን ከሁለቱ ተቋማት የተውጣጡ 29 ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።

1t8a7809
1t8a7864.jpg
1t8a7847.jpg
1t8a7891.jpg