ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከጥቅምት 18/2015ዓ.ም እስከ ሰኔ 27/2017ዓ.ም ድረስ በኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ ለቆዩትና ከሰኔ 25/2017ዓ.ም ጀምሮ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ለተሾሙት አቶ ሙሉቀን ቀሬ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የሽኝት ፕሮግራም ተደረገ።

በተቋሙ ከፍተኛ አመራርና ሠራተኞች በተዘጋጀ የሽኝት ፕሮግራም ላይ የተገኙት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በረከት ፍስሀ ፅዮንና የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ በተቋሙ ቆይታቸው ለሰጡት የላቀ አመራርና ላሳዩት ትጋት ምስጋናቸውን አቅርበው ቀጣይ የስራ ጊዜያቸው የተሳካ እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።



