
ጳጉሜ 1/2017ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስትቲስቲክስ አገልግሎት ከፌዴራል ፣ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና ከሁሉም ክልል ፕላንና ልማት፣ የንግድና ገበያ ልማት ፣ ከገቢዎች፣ ከኮንስትራክሽንና ከኢንዱስትሪ ቢሮ ለተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በ2018 ዓ.ም ለሚካሄደው የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለፍሬሚንግ ግብዓትነት የሚውሉ አስተዳደራዊ መረጃ አቅርቦት ላይ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በ2018 የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ከገጠር ለሚሰበሰቡት መረጃዎች ፍሬሚንግ የሚውል አስተዳደራዊ መረጃ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ መሆኑን አንስተው የሚፈለገው መረጃ በአግባቡ ቀርቦ ለታሰበው አገልግሎት ማዋል እንዲቻል ከፌዴራል፣ ከከተማ አስተዳደርና ከሁሉም ክልል የመጣችሁ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጠንካራ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልፀው ለስራው መሳካት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ስለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የሚመለከት ገለፃ በቢዝነስ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ናቃቸው ነጋሽ ቀርቦ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ የተሰራ ሲሆን ስልጠናው አስተዳደራዊ መረጃ ለመስክ ስራ ፍሬም አስፈላጊነት ላይ ለቀጣይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።



