
ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት ወደ ኢትዮጵያ ለመጡት የኮሪያ ስታቲስቲክስ ልዑካን ቡድን ስለተቋሙ ግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ ተደረገ።

የልዑክ ቡድኑን ለመቀበል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የተቋሙ ከምስረታው ጀምሮ አሁን እስከ ደረሰበት ደረጀ ያለፈባቸውን ተቋማዊ ጉዞ፣ በሂደቱም የተገኙ ውጤቶች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጨ ላይ ገለፃ ያቀረቡት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር ሜሮን ክፈለው ተቋሙ ባላፉት ሁለት ዓመታት እያካሄደ በሚገኘው ተቋማዊ ሪፎርም መረጃ ከመሰብሰብ እስከ ሪፖርት ዝግጅት ያለውን ሂደት ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ለማድረግ እየተገበረ የሚገኘው አሰራር የበለጠ ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በተደረገላቸው ገለጻ ስለተቋሙ የተሟላ ግንዛቤ እንዳገኙ የቡድኑ አባላቱ ገልፀዋል።