
ነሐሴ 6/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኮሪያ ስታቲስቲክስ ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የቱሪስት ማዕከላትን እንዲጎበኙ ተደረገ።

በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ የሚገኘው የኮሪያ ስታቲስቲክስ ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የቱሪስት ማዕከላትን እንዲጎበኙ በተቋሙ በተዘጋጀ ፕሮግራም አድዋ ሙዚየም፣ ወዳጅነትና እንጦጦ ፓርክን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ወቅት በፓርኮችና በከተማ ውስጥ ባዩት ሁሉ ደስተኛ መሆናቸውን የከተማዋን ዋና የቱሪስት መዳረሻዎች በማወቃቸው ወደሀገራቸው ሲመለሱ ሰዎች ወደ ከተማዋ ለጉብኝት እንዲመጡ ለማስተዋወቅ ግንዛቤ እንዳገኙ የልዑካን ቡድን አባላቱ ገልፀዋል።
