ህዳር 30/2017ዓ.ም፣በአምስተኛ ዙር የስነ-ህዝብና ጤና ጥናት የመስክ ስራ አፈፃፀም ላይ መቀመጫውን አሜርካን ሀገር ካደረገው ከ(Inter City Fund (ICF)) ተወካይ ዶ/ር ሊቪያ ሞንታና ጋር በዋናው መስሪያ ቤት ውይይት ተደረገ።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ የስነ-ህዝብ ጤና ጥናት የመስክ ስራ አሁን የደረሰበት ደረጃ እና በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለማጠናቀቅ እያተሠራ መሆኑን በማስረዳት ስራው አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ በ(Inter City Fund (ICF)) እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ለተደረገ የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ በተቋሙ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዶ/ር ሊቪያ ሞንታና በስነ-ህዝብና ጤና ጥናት ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጋር ከአስር ዓመታት በላይ በጋራ መስራታቸውን ገልፀው፤ ከጥናቱ የሚገኙ መረጃዎች ለጤናው ዘርፍ እቅድ፣ ለፖሊሲ ቀረፃ የሚውል በመሆናቸው የሚሰበሰቡ መረጃዎች አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና ጥራት ያላቸው መሆናቸውን ማረገጋጥ አስፈላጊ ነው ሲሉ አንስተው ተቋማቸው ጥናቱ እስከሚጠናቀቅ ድጋፋን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።