የካቲት 02/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ አስተዳደር በሚያከናውነው የቆጠራ ቦታ ካርታ አፕዴቲንግ ስራ ምንነትና አስፈላጊነት ላይ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተማዎች ለተውጣጡ የፕላንና ልማት፣ የከንቲባ ጽ/ቤትና የሥራና ክህሎት ቢሮ የስራ ኃላፊዎች በቢሾፍቱ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ የዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር ሜሮን ክፈለው በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በየጊዜው በተካሄዱ የአስተዳደራዊ ይዘት ለውጥ ምክንያት ከዚህ ቀደም የተሠሩትን የቆጠራ ቦታ ካርታዎችን ለአሁናዊ የስታቲስቲክስ ተግባራት በሚሆን መልኩ እንደአዲስ ማካለል አስፈላጊ መሆኑን በማስረዳት፣ ስራውን ለማሳካት የየከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ድጋፍ እና ትኩረት የሚጠይቅ በመሆኑ፣ በጉዳዩ ላይ የጋራ መረዳት እንዲፈጠር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።


የተቋሙ አሁናዊ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ እና የቆጠራ ካርታ ምንነትና አስፈላጊነት ላይ ገለፃ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመድረኩ የተሳተፉት የሥራ ኃላፊዎች በቀረበላቸው ገለፃ ስለተቋሙ አሁናዊ የሥራ እንቅስቃሴ በቂ ግንዛቤ እንዳገኙ እና በየከተማቸው ለሚካሄደው የቆጠራ ቦታ ካርታ አፕዴቲንግ ሥራ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።


