በተቋሙ በተዘጋጀው የዕውቀት ግብይት መድረክ ላይ ነባር ዕውቀቶች ቀርበው ግንዛቤ ተፈጥሮበታል

ታህሣሥ 21/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

1t8a7876

በተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ የዕውቀት ሽግግር መድረክ ተዘጋጅቶ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ተሠርቷል።

1t8a7895 3

የተቋሙ የስታቲስቲክስ መረጃ ስርጭት እና ተደራሽነት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ትግስት በቀለ በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የሥራ ክፍሎች ማንኛውንም ዕውቀት በአግባቡ መሰነድ እንዳለባቸው አንስተው፣ የዕውቀት ሽግግር የተቋሙ ባህል በማድረግ፣ ዕውቀትን መለዋወጥ እና ለተተኪ ትውልድ በተደራጀ መልኩ ማስተላለፍ የመድረኩ ዋና ዓላማ መሆኑን ገልፀዋል።

1t8a7909

በተዘጋጀው መድረክ ላይ በሥነ-ሕዝብ እና ጤና ጥናት፣ የሰው ሀብት አስተዳደር መረጃ አያያዝ እና የICT አጠቃቀም ፖሊሲን በተመለከተ ነባር ዕውቀቶች ላይ ገለጻ ቀርቦ ግንዛቤ የተፈጠረበት ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎች የእውቀት ግብይት መድረኩ መዘጋጀቱ ለልምድና ለዕውቀት ሽግግር ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው መድረኩ ቀጣይነት እንዲኖረው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

1t8a7927
1t8a7926