በክልሉ በአዲስ የተደራጁትን ወረዳዎች ያማከለ የቆጠራ ቦታ ማዘጋጀት በሚቻልበት ሁኔታላይ ውይይት ተደረገ

ታህሳስ 23/04/2017 ዓ.ም፣ በአፉር ክልል በአዲስ የተደራጁ የወረዳና የቀበሌ አደረጃጀት ያማከለ የቆጠራ ቦታዎችን ማዘጋጀት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የክልሉ የፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀሚዲ ዱላ በተገኙ መድረክ በሰመራ ውይይት ተደረገ።

ክልሉ አዲስ ያደራጀውን የወረዳና ቀበሌ አደረጃጀት መሠረት ያደረገ የቆጠራ ቦታ ካርታ እንዲዘጋጅላቸው ለተቋማቸው ያቀረበውን ተገቢ ጥያቄ ለመመለስ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ በመወያየት ፈጣን ምላሻ ለመስጠት የተቋማቸው የካርቶግራፊና ጂአይኤስ ቡድን ይዘው በክልሉ መገኘታቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ምትክል ዋና ደይሬክተር ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ ቡድኑ ስራውን በአጠረ ጊዜ እንዲያጠናቅቅ ክልሉ ለስራው የሚያስፈልጉት መረጃዎች በማቅረብ፣ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚጠቅባቸው አስረድተዋል።

የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀሚዲ ዱላ ተቋሙ ክልላቸው ያቀረበውን ጥያቄ ተገቢነት ተቀብሎ ለሰጠው ፈጠን ምላሽ በክልሉ መንግስትና በራሳቸው ስም ያላቸውን ምስጋና አቅርበው ለስራው ለተመደበው ቡድን አስፈላጊውን መረጃ በማቅረብ እንዲሁም ሌሎችንም ድጋፍ የሚያደርግ ቡድን እንደሚያደራጅና ስራው በታቀደ ጊዜ እንዲጠናቀቅ ክትትል እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።