በግብርና ቆጠራ ላይ ውይይት ተደረገ

ታህሳስ 24/2017ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017ዓ.ም እያካሄደ በሚገኘው የግብርና ቆጠራ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ቢሮ ጋር ውይይት አደረገ።

በውይይቱ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የተገኙ ሲሆን ከግብርና ቆጠራ የሚገኘው መረጃ ለሀገር ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት የተጀመረውን የግብርና ቆጠራ በጋራ በማሳካት ጥራት ያለውና ተዓማኒ መረጃ ለተጠቃሚው ማቅረብ አለብን ሲሉ ገልፀዋል።

በውይይት መድረኩ የግብርና ቆጠራ ከቅድመ ዝግጅት አሁን እስከደረሰበት ያለውን አፈፃፀም የሚያሳይ ገለፃ በግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱላዚዝ ሽፋ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ እና የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል።