በ2018 የሀገራዊ ልማት እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ

ሐምሌ 16/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

1g7a8888


የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በ2018ዓ.ም ሀገራዊ የልማት እቅድ ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደረገ።

1t8a3987.jpg


የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በሀገራችን በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑን አንስተው በ2018 በጀት ዓመት ቀጣይነት ያለው እድገት ለማስመዝገብ ዓለም አቀፍ አዝማሚያዎችን ታሳቢ ያደረገ የእቅድ ዝግጅት መደረጉን፤ በ2018 በጀት ዓመት የዋጋ ግሽበትን ወደ አንድ አሀዝ ለመቀነስና የሀገሪቷ እድገት ዘጠኝ በመቶ ለማድረስ መታቀዱን ገልፀዋል።

1t8a3991.jpg


በመድረኩ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ በሆኑት አቶ ፃድቃን አለማየሁ በሁሉም ዘርፎች በ2017 በጀት ዓመት የተመዘገቡ አፈፃፀሞችና በ2018 በጀት ዓመት የታቀዱ እቅዶችና በቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ቀርቦ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የተቋማቱ ሰራተኞችም በ2017 የተገኙትን ውጤቶች በማስቀጠል በአዲሱ በጀት ዓመት በትጋት እንደሚሰሩ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

1t8a3996.jpg