ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት የመስክ ስራ ተጠናቀቀ

መስከረም 27/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከመስከረም 10/2017ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ከመላ ሀገሪቱ ገጠርና ከተማ በተመረጡ 2,881 የቆጠራ ቦታዎች ሲካሄድ የነበረው ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት የመስክ ስራ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለፀ።

1t8a0066 2

የመስክ ስራ መጠናቀቁን በማስመልከት በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በተሰጠው መግለጫ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የጥናቱ የመስክ ስራ በታቀደው መሰረት እንዲጠናቀቅ ለሰሩት የተቋሙ ሰራተኞች፣ ድጋፍ ላደረጉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ከጥናቱ የተገኙትን መረጃዎች የማጥራትና የማጠናቀር ስራ በማጠናቀቅ በአጭር ጊዜ የመጀመሪያ የጥናቱን ሪፖርት ወጤት ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ በትጋት መስራት እንደሚገባቸው ለስራ ክፍሉ ከፍተኛ ባለሙያዎች የስር መመሪያ ሰጥተዋል።

1t8a0080