ተቋማቱ በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

1t8a0756


የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በዓለም ባንክ ድጋፍ በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በገጠር መንገድ ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የሚሰሩትን የገጠር መንገድ ግንባታ ስራዎች መሰራታቸውን ለማረጋገጥ (Verification) የሚያስችል ስራ ለመስራት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ስምምነት ተፈራረመ።

1t8a0844
1t8a0794


የስምምነት ሰነዱን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ የትምጌታ አስራት እና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የተፈራረሙ ሲሆን የተሰጣቸውን ሀላፊነት በጥራትና በታማኝነት በተባለው ጊዜ አጠናቀው ለማስረከብ እንደሚሰሩ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

1t8a0766


የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በብቁ ባለሙያዎች የተደራጀና የካበት ልምድ ካላቸው የሀገራችን ተቋማት አንዱ መሆኑን አንስተው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተከናወነ የሚገኘውን የገጠር መንገዶች ተደራሽነት ፕሮጀክት የማረጋገጥ (Verification) ስራውን በጥራትና በብቃት እንደሚወጣ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

1t8a0768
1t8a0858